ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በምክር ቤቶች የጋራ ስብስባ ያደረጉት ንግግር የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ነው ተባለ

ጥቅምት 8/2015 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 30፣ 2015 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉት የመክፈቻ ንግግር የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

በዛሬው ዕለት 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብስባ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ለሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበውን የድጋፍ ሞሽን አዳምጧል፡፡

የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ የድጋፍ ሞሽኑን ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት የፕሬዚዳንቷ የመክፈቻ ንግግር የፌዴራል መንግስቱን ዓመታዊ ዕቅድ የዳሰሰና የንግግሩ ይዘት መንግስት በ2015 ሊያከናውናቸው የሚገቡ ዐበይት ተግባራትን ያካተተ መሆኑን አስታውሰዋል።

የድጋፍ ሞሽኑ ቀጣይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ውይይት ተደርጎበት የሚጸድቅ ሲሆን ውይይት የሚደረግበት ጊዜ ወደ ፊት የሚገለጽ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ አስታውቀዋል፡፡

የምከር ቤቱ 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ-ጉባዔ በአንድ ድምጽ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ መጽደቁን የምክር ቤቱ መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW