ባለስልጣኑ አገልግሎቱን ለማዘመን እና የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ ከዓለም ባንክ ጋር እየሰራ መሆኑን ገለጸ

ጥቅምት 9/2015 (ዋልታ) የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አገልግሎቱን ለማዘመን እና የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ ከዓለም ባንክ ጋር እየሰራ መሆኑን ገለጸ።

ባለስልጣኑ ከዓለም ባንክ ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።

የምክክር መድረኩ የፋይናንስ ሥርዓቱን በማዘመን ቀልጣፋና ግልፅ አሰራር ከዓለም ባንክ እና ሌሎች አጋር ድርጂቶች በመተባበር ለመስራት ያለመ ነው ተብሏል።

የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀጂ ኢብሳ ከመንግሥት በጀት ውስጥ 65 በመቶ የሚሆነውን ለመንግስት ግዥና ንብረት እንደሚውል ገልፀው አገልግሎቱን ለማዘመን እና የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ በጋራ እየሰራን ነው ብለዋል።

በብርቱካን መልካሙ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW