የቱሪዝም ቀን “አዲስ እሳቤ ለቱሪዝም” በሚል መሪ ቃል ይከበራል

ጥቅምት 11/2015 (ዋልታ) የዘንድሮው የቱሪዝም ቀን በአለም ለ43ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ35ኛ ጊዜ “አዲስ እሳቤ ለቱሪዝም” በሚል መሪ ቃል ይከበራል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የዓለም ቱሪዝም ቀንን በማስመልከት ሲምፖዚየም ተካሂዷል።

የቢሮው ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ፒኤችዲ) ቱሪዝሙ የገጠሙትን ተግዳሮቶች በመቋቋም በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተው የዘንድሮ የቱሪዝም  ቀንን ስናከብርም  መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት በመደገፍ በአዲስ እይታ ዘርፉን ለማሳደግ ለመስራት ቃል በመግባት ነው ብለዋል።

አዲስ አበባ የቱሪስት መዳረሻም መስህብም ናት ያሉ ሲሆን ከማክሰኞ ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም አንስቶ ለሶስት ቀናት ይከበራል ሲሉ ጠቁመዋል።

በብርቱካን መልካሙ