ኢመደአ ለአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የጸረ ስለላ ቴክኒካል አገልግሎት ሊሰጥ ነው

ጥቅምት 15/2015 (ዋልታ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የጸረ ስለላ ቴክኒካል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ስምምነት ፈጸመ።

ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የውል ስምምነት ተፈራረሙ

ስምምነቱ አካዳሚው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶችና አጠቃላይ የአካዳሚውን የሥራ ቦታ ለየትኛውም አይነት የኤሌክትሮኒክስ ስለላ ሊያጋልጡ የሚችሉ ክፍተቶችንና ተጋላጭነቶችን ለመከላከል የሚያስችል የጸረ ስለላ ቴክኒካል አገልግሎት መሰጠት ነው ተብሏል።

በስምምነቱ ላይ የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር ዳንኤል ጉታ፣ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ከኢንፎርሜሽን ጥቃት ለመከላከልና ደህንነቱን ለማስጠበቅ የሚያስችል የጸረ ስለላ ቴክኒካል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የቴክኖሎጂ አቅምም ይሁን ብቃት ያለው የሰው ሃይል ኢመደአ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

አካዳሚው የኢንፎርሜሽን ደህንነቱን ለማረጋገጥ ያስችለው ዘንድ ይህንን አገልግሎት ከኢመደአ ለማግኘት የወሰደው ቁርጠኝነት ለሌሎች ተቋማትም ጭምር አርአያ እንደሆነ መጠቆማቸውን የአገልግሎቱ መረጃ አመላክቷል።