ኢትዮ ቴሌኮም “ቴሌ ክላውድ” የተሰኘ አገልግሎት አስጀመረ

“ቴሌ ክላውድ”

ጥቅምት 17/2015 (ዋልታ) ኢትዮ ቴሌኮም “ቴሌ ክላውድ” የተሰኘ ተቋማት የተለያዩ መረጃዎችን የትም መሄድ ሳይጠበቅባቸው በኢትዮ ቴሌኮም ዳታ ቤዝ ላይ የሚያገኙበት አሰራር ይፋ አድርጓል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በአገልግሎቱ ተቋማት የዳታ ሴንተር ወይም የመረጃ ማዕከል መገንባት ሳይጠበቅባቸው የፈለጉትን መረጃ ከኢትዮ ቴሌኮም ማግኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል።

አገልግሎቱ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ምርታማነትን የሚያሳድግ እንደሆነም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም የመረጃ ማዕከል በመገንባት ለተቋማት ማከራየት እንደጀመረ የገለጹት ስራ አስፈፃሚዋ ተቋም ስንመራ ከሚያጋጥሙን ችግሮች መካከል ዳታ ሴንተር መገንባት እንደሆነና ይህንን መረጃ ማዕከል ተቋማት እስኪያገኙ ድረስ ኢትዮ ቴሌኮም መፍትሄ ይዞ መምጣቱን ገልፀዋል።

ቴሌ ክላውድ በርካታ ጥቅሞች እንዳሉና የመጀመሪያው infrastrcture as a service የተሰኘ ሲሆን ተቋማት አፕልኬሽንና ዳታ ይዞ በመምጣት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ አመላክተዋል።

ከአይቲ ጋር ተያይዘው የሚወጡ ወጪዎችን ለመቀነስ እንደሚረዳም ነው ስራ አስፈፃሚዋ የገለጹት።

ሁለተኛው አገልግሎት platform as a service የተሰኘ አገልግሎት ይዞ እንደመጣ ያስታወቀው ኢትዮ ቴሌኮም የትኛውንም መረጃ ማግኘት ከኢትዮ ቴሌኮም የምንችልበት ነው ብሏል።

ሦስተኛው Software as a service የተሰኘ ሲሆን ተቋማት ባሉበት ሆነው አገልግሎታቸውን በቪዲዮ መቆጣጠር የሚችሉበት አሰራር እንደሆነም ተቋሙ አስታውቋል።

በሱራፌል መንግስቴ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW