9ኛው የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ስነሥርዓት ጥቅምት 19 እንደሚካሄድ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት በዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመ ሲሆን ዘጠነኛው የጥራት ሽልማት ስነሥርዓት ጥቅምት 19 እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ሽልማቱ በጥራት የላቁና የአለም ገበያን መቆጣጠር የሚችሉ አምራቾችን እንዲሁም ተቋማትን ለማጎልበት ይረዳል ተብሏል።

ባለፉት አመታት 446 ድርጅቶችና ተቋማት በኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ውድድር መሳተፋቸው የተገለፀ ሲሆን፤ በዘንድሮ ዓመትም 40 ድርጅቶች በ7 ዘርፎች እንደሚወዳደሩም ተጠቁሟል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጣሰው ወልደሃና (ፕ/ር)  ሽልማቱ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ምርቶች ያላቸው ተቋማትን ለማጎልበት ያግዛል ብለዋል።

የሽልማት ስነሥርአቱ በታላቁ ቤተ መንግስት የሚከናወን ሲሆን በዋልታ ቴሌቪዥን በቀጥታ ሥርጭት ይተላለፋል።

ብሩክታይት አፈሩ