የመጀመሪያው የአፍሪካ ወጣቶች ጉባዔ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

ጥቅምት 17/2015 (ዋልታ) የመጀመሪያው የአፍሪካ ወጣቶች ጉባዔ በአዲስ አበባ ከጥቅምት 19 እስከ 21/2015 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገለጸ።

ጉባኤው “Integrated Africa the bridge of PM Abiy Ahmed” በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚካሄድም ነው የተገለጸው።

በጉባኤው ከ50 በላይ የአፍሪካ ሀገራት የሚመጡ ወጣት አመራሮች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ጉባኤው የሚካሄደው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሀሳብ አመንጭነት ሲሆን የአፍሪካዊያን ወንድማማችነት ማጠናከርን ዓላማ ያደረገ ነው ተብሏል።

በመስከረም ቸርነት

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW