ሩሲያ፤ የሰላም ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ሰላምና ብልጽግና መሰረት እንደሚጥል አስታወቀች

ጥቅምት 24/2015 (ዋልታ ) ሩሲያ የፌደራል መንግስትና ሕወሓት የተፈራረሙት የሰላም ስምምነት ለኢትዮጵያ ሰላምና ብልጽግና መሰረት እንደሚጥል ገልጻለች።

በአዲስ አበባ የሩሲያ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ስምምነቱ ኢትዮጵያውያን እርቅ እንዲፈጥሩ ወሳኝ ሚና ይኖረዋልም ብሏል።

መግለጫው በፌደራል መንግስትና ሕወሓት መካከል የተፈረመው ስምምነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋምና ኢትዮጵያውያን ሰላማቸውን አረጋጥጠው ወደ ብልጽግና እንዲጓዙ ጠንካራ መሰረት የሚጥል እንደሆነ አመልክቷል።