የደረቅ ቆሻሻን መልሶ በማልማት ከ4 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘት ተችሏል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ጥቅምት 27/2015 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ የደረቅ ቆሻሻ በመሰብሰብና መልሶ በማልማት ተግባር ባለፉት ሁለት አመታት ከ4 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።
ከንቲባዋ ይህንን ያሉት በቆሻሻ መልሶ ማልማትና በዘላቂ አመጋገብ እና የስነምግብ ዘርፍ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ዕውቅና የመስጠት መርሀ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
ከንቲባዋ በመዲናችን 13 የምገባ ማዕከላትን በመገንባት በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን መመገብ እንደተቻለ ነው የገለጹት።
በየተማሪዎች ምገባ መርሀግብር የትምህርት መጠነ ማቋረጥን የቀነሰ ሲሆን በምግብ እጦት ራሳቸውን የሚስቱ ተማሪዎች በአግባቡ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ማስቻሉን አንስተዋል።
ይህም በደረቅ ቆሻሻ መልሶ ማልማትና የምገባ መርሀ ግብር ተሞክሮዎች ምክንያት አዲስ አበባ በአለም አቀፍ ደረጃ ሁለት ሽልማቶች ማግኘት አስችሏታል ነው ያሉት።
ሽልማቱ የመላው አፍሪካዊያን፣ በአዲስ አበባ ተቀማጭነታቸውን ያደረጉ አለም አቀፍ ማህበረሰቦችም ጭምር ስለመሆኑ ተናግረው፤ በአለም አቀፍ ደረጃ አዲስ አበባ ተወዳዳሪ ከተማ በመሆንዋም እንኳን ደስ ያለን ብለዋል።
በሰለሞን በየነ