ኮሚሽኑ በመጀመሬያ ሩብ ዓመት በ202 መዛግብት ውሳኔ መስጠቱን አስታወቀ

ጥቅምት 29/2015 (ዋልታ) የፌዴራል ታስክ ይግባኝ ኮሚሽን በ2015 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በ202 መዛግብት ላይ ውሳኔ በመስጠት መቶ በመቶ አፈፃፀም ማስመዝገቡን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ የ2015 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ያከናወናቸውን ተግባራት ገለፃ አድርጓል።

በሩብ ዓመቱ ለውሳኔ ከተቀጠሩት 202 መዛግብት ሙሉ በሙሉ ውሳኔ በመስጠት የተሟላ አፈፃፀም ተመዝግቧል ተብሏል።

የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ሙሉጌታ አያሌው በሰጡት መግለጫ ኮሚሽኑ የግብር ከፋዮችን ቅሬታ በመሰብሰብ ቅሬታ በቀረበ በ120 ቀናት ውስጥ ፍትሃዊ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ኮሚሽኑ ዘመናዊ የዳታ ቤዝ ሥርአትን በመዘርጋት ህብረተሰቡ በያለበት ሆኖ የኦንላይን መረጃ እንዲያግኝና መመዝገብ እንዲችሉ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በብሩክታይት አፈሩ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW