የሰላም ስምምነቱን አስመልክቶ ለወታደራዊ አታሼዎች ማብራሪያ ተሰጠ

ኅዳር 6/2015 (ዋልታ) በኢትዮጵያ መንግስትና በህውሃት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ማብራሪያውን እየተሰጠ የሚገኘው በመከላከያ ሚኒስቴር የውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክቶሬት ነው።

የሰላም ስምምነቱ ወደ ተግባር መቀየር እንዲቻለ የሁሉም ሀገራት ትብብር እንደሚያስፈልግ ነው የተነሳው።

ማብራሪያውን የሰጡት በመከላከያ ሚኒስቴር የውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክተር ጀነራል ሜጀር ጀነራል ተሾመ ገመቹ ናቸው።

ሜጀር ጄነራል ተሾመ ዛሬ ኢትዮጵያ በአዲስ የተስፋ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች ያሉ ሲሆን የሰላም ስምምነቱ ግጭትን በዘላቂነት የማስቆም ስምምነት ነው ብለዋል።

በማብራሪያቸውም የሰብዓዊ ድጋፍ በተቀመጠለት መንገድ እንዲደርስ የሚያደርገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን አንስተዋል።

በአሁን ግዜም ሰራዊቱ በትግራይ ክልል የተለያዩ ማህበራዊ ኃላፊነቶችን እየተወጣም እንደሚገኝ አንስተዋል።

የተደረሰው የሰላም ስምምነት ውጤታማ እንዲሆን ሀገራቱ ትብብር እንደሚያደርጉም በዚሁ ግዜ ተገልጿል።

በሰለሞን በየነ