16ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ወር ተከበረ

ኅዳር 8/2015 (ዋልታ) “የወጣቶች ንቁ ተሳትፎና ተካታችነት ለስብዕና ልማት” በሚል መሪ ሀሳብ 16ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ወር በአሶሳ ከተማ ተከበረ።

በኢትዮጵያ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አዘጋጅነት የሚከበረው የአፍሪካ ወጣቶች ወር ወጣትና ስራ ፈጣሪነት ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ወጣቶች በቁጥር ምጣኔ ረገድ ካላቸው ከፍተኛ ድርሻ ሁለንተናዊ የበቃ ተሳትፎን በማካተት የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ እንዲያገኙ ዓለም ዐቀፍና አህጉር ዐቀፍ ኩነቶችን በተለያዩ ዝግጅቶች በማክበር የግንዛቤ መፍጠሪያ ስራዎችም እየተሰሩ ነው፡፡

የአፍሪካ ወጣቶች ወር የመጀመሪያው ሳምንት በአርባ ምንጭ የተከበረ ሲሆን በሁለተኛው ሳምንት በአሶሳ በማክበር ቀጣዩን በጋምቤላ ክልል እንዲሁም ማጠቃለያው ደግሞ በድሬዳዋ ይሆናል።

ግዛቸው ይገረሙ (ከአሶሳ)