አብረን ስንሆን እናምራለን፤ ኢትዮጵያችንም ከፍ ትላለች – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የኅዳር 11/2015 (ዋልታ) አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አብሮነት ውበት መሆኑን እና ኢትዮጵያንም ከፍ እንደሚያደርጋት ተናገሩ።
ከንቲባዋ የከተማዋ ድምቀት እና ውበት የሆነው የ2015 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የ10 ኪሎሜትር ውድድርን አስጀምረዋል።
“ታላቁ ሩጫ ከስፖርታዊ ውድድርነቱም ባሻገር የአብሮነት፣ የሰላም እና የፍቅር እንዲሁም የትብብር ተምሳሌት ጭምር መሆኑን ነው የገለጹት።
ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ለውድድሩ አዘጋጆች፣ በውድድሩ ለተሳተፉት እና አሸናፊ ለሆኑት በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።