የሀገር ሽማግሌዎች ከጥንት ጀምሮ አለመግባባቶችን በመፍታት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተጠቆመ

ኀዳር 12/2015 (ዋልታ) የሀገር ሽማግሌዎች ከጥንት ጀምሮ በሀገሪቱ በሚያጋጥሙ አለመግባባቶች ዙሪያ ባህልን፣ ወግን እንዲሁም እምነትን ባከበረ መልኩ ለሰላም ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከታቸዉን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽኑ የተቋቋመበትን አላማ ከግብ ለማድረስ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከተወጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር እየመከረ ይገኛል፡፡
እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ የሽምግልና ባህል የኢትዮጵያ አንዱ መገለጫ መሆኑን አንስተው አሁን ላይም በሀገሪቱ የተጀመረውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ የሀገር ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ ሊሆን እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
በሀገሪቱ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለመቅረፍ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በጋራ መስራት እንዳለባቸዉ ተጠቁሟል፡፡
ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸዉን ተግባራት እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡
በአመለወርቅ መኳንንት