በክልሉ በበጋ መስኖ ከ41 ሺሕ ሄክታር በላይ መሬት የቆላ ስንዴ ለማልማት እየተሰራ ነው

ታኅሣሥ 11/2015 (ዋልታ) በአፋር ክልል በበጋ መስኖ ከ41 ሺሕ 900 ሄክታር በላይ መሬት ላይ የቆላ ስንዴ ማልማት የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ እንስሳት፣ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው የሰብል ልማት ከፍተኛ ባለሙያ አለማየሁ ተፈሪ በክልሉ በበጋ መስኖ የቆላ ስንዴን በስፋት ለማልማት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው በዞን አንድና ሦስት በሚገኙ 10 ወረዳዎች እቅዱ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

እስካሁን ታርሶ ከተዘጋጀው ከ10 ሺሕ 500 ሄክታር መሬት ውስጥ ከ5 ሺሕ በላይ በዘር መሸፈኑን የተናገሩት ባለሙያው የስንዴ ልማቱ በባለሃብቶች፣ በከፊል አርብቶ አደሮችና በማህበር በተደራጁ ወጣቶች አማካኝነት እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።

በአፋር ክልል በዘንድሮ በጋ ወራት ከ102 ሺሕ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ስንዴን ጨምሮ ጥጥ፣ በቆሎ፣ ማሽላና ማሾ ሰብሎችን ለማልማት ታቅዶ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured