ሚኒስትሩ የሰላም ሂደቱ ለማመንታት እድል በማይሰጥ መልኩ በፍጥነት ወደ ፊት እየሄደ ነው አሉ

አብርሃም በላይ (ዶ/ር)

ታኅሣሥ 19/2015 (ዋልታ) የሰላም ሂደቱ ለማመንታት እድል በማይሰጥ መልኩ ሦስት እርምጃ ወደ ፊት እየሄደና አዎንታዊ ምላሽ እያገኘ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ እንገለጹት የሰላም እርምጃ ልምምድ የወጣ ተግባር መፈጸምን ይጠይቃል።

“አሁንም ከባድ ውጣ ውረድና በልዩ የመሪነት ብቃት ታልፎ፣ የሰላም ሂደቱ ለማመንታት እድል በማይሰጥ መልኩ በፍጥነት ሦስት እርምጃ ወደ ፊት እየሄደና አዎንታዊ ምላሽ እየያዘ ይገኛል” ብለዋል።

የሰላም አምባሳደር የልኡካን ቡድንም የፈፀመው የሰላም ግንባር ጀግንነት በመላው ህዝባችን ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪዬን አቀርባለሁ ሲሉም አክለዋል።