ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር እየተወያዩ ነው


ጥር 16/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “በምሁራን አገራዊ ሚና” ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር እየተወያዩ ይገኛሉ።

ከዚህ በፊት “በአገረ-መንግሥት ግንባታ የምሁራን ሚና” በሚል መሪ ሐሳብ በተለያዩ ቦታዎች በርካታ የምክክር መድረኮች መደረጋቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር “ለሀገር ብልጽግና የምሁራን ሚና” በሚል መሪ ሐሳብ እየተወያዩ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ በፊት በተደረጉ የውይይት መድረኮች ምሁራን በአገር ግንባታ ላይ የሚኖራቸውን ሚና ለመጫወት ፍላጎት እንዳላቸው መረዳታቸውን ገልጸዋል።

የዕለቱ የውይይት መድረክ ዋና መሻትም የምሁራንን ዕውቀት ለአገር ግንባታ ከማዋል ጽኑ ፍላጎት የተነሳ መሆኑን አንሥተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።