በአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ የሚሳተፉ የተለያዩ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባት ጀመሩ

የካቲት 7/2015 (ዋልታ) በ42ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የሚሳተፉ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።

በየአገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚስትሮች የተመራው ልዑካን ቡድን ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

እስካሁን  የሶማሊያ፣ ሴራሊዮን፣ ናይጄሪያ፣ ኮትዲቭዋር፣ ታንዛኒያ፣ ማሊ፣ ዚምባብዌ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ኢስዋቲኒ፣ ኮሞሮስ እና የቦትስዋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና ልዑካን ቡድኖቻቸው አዲስ አበባ ገብተዋል።

በአስፈፃሚ ምክር ቤት በስብሰባ ላይ የሚሳተፉ የሌሎች አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የልዑካን ቡድኖቻቸውም አዲስ አበባ በመግባት ላይ እንደሚገኙ የኢዜአ ዘገባ አመላክቷል።

36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚካሄድ ይሆናል።