ሚኒስቴሩ እና ዓለም ባንክ በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመስራት ውይይት አደረጉ 

የካቲት 7/2015 (ዋልታ) የፕላንና ልማት ሚኒስቴር እና ዓለም ባንክ በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመስራት የሚያስችል ዉይይት አድርገዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) የዓለም ባንክ የልዑካን ቡድን አባላትን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ተግባራትን በመለየት በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተገልጿል።

ዓለም ባንክ የኢትዮጵያን ልማት በማገዝና በመደገፍ ከፍተኛ ሚና ያለው መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሯ ይህም ድጋፍ በጋራ የልማት ስራዎችን በመተግበር እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኡስማን ዲዮን በበኩላቸው ባንኩ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያን እድገት ለማፋጠን መንግስት የሚያከናውናቸውን የልማት ተግባራት በመደገፍ ሲያከናውናቸው የነበሩ ተግባራትን አጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።