ኢትዮጵያ እና ኬንያ የጸጥታ ስጋቶችን በጋራ ለመከላከል ተስማሙ

የካቲት 30/2015 (ዋልታ) ኢትዮጵያ እና ኬንያ በአገራቱ የጋራ ድንበር አካባቢ የሚከሰቱ የጸጥታ ስጋቶችን በቅንጅት ለመከላከል ተስማሙ፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ የተመራ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ ከኬንያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በናይሮቢ መወያየታቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

በውይይታቸውም ሁለቱ አገራት በጸጥታው ዘርፍ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሀገራቱ የጋራ ድንበር አካባቢ የሚከሰቱ የጸጥታ ስጋቶችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸውንም አመልክተዋል፡፡