በሩሲያ ጥቃት የአውሮፓ ትልቁ የኒውክሌር ማብላያ ማዕከል የኃይል መቋረጥ ገጠመው

የካቲት 30/2015 (ዋልታ) ሩሲያ በዩክሬን ከተሞች ላይ የምታደርገው የሚሳኤል ጥቃት አጠናክራ ስትቀጥል ጥቃቱ በበርካታ ከተሞች የመሰረተ ልማት ውድመትን አስከትሏል፡፡

ሩሲያ ከ83 በላይ ሚሳኤሎች ወደ ዩክሬን ያስወነጨፈች ሲሆን በጥቃቱ የዛፖሪዝሂያ የኒውክሌር ኃይል ማብላያ ማዕከል የኃይል መቆራረጥ ገጥሞታል፡፡

እንደቢቢሲ ዘገባ በጥቃቱ እስካሁን ዘጠኝ ሰዎች የሞቱ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል፡፡

የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ግሮሲ የዛፖሪዝሂያ የኒውክሌር ኃይል ማብላያ ማዕከል ትኩረት መነፈጉ አሳሳቢ መሆኑን ለሮይተርስ ገልጸዋል፡፡

ሁሉም አካላት ይህንን የኒውክሌር ማብላያ ደህንነት ለመጠበቅ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ያሉት ግሮሲ ለዚህም በቁርጠኝነት ወደ ተግባር መግባት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡