ሜንሽን ፎር ሜንሽን ለቦረና ድርቅ ተጎጂዎች 100 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

ሚያዝያ 3/2015 (ዋልታ) ሜንሽን ፎር ሜንሽን ለቦረና ድርቅ ተጎጂዎች 100 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ፡፡

ድርጅቱ ሕብረተሰቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከችግር ተላቆ በምግብ ራሱን እንዲችል ለማድረግም በሦስት ወር የሚደርስ 200 ኩንታል በቆሎ እና 1000 ኩንታል ማዳበሪያ ገዝቶ ለማከፋፈል ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል፡፡

ድጋፉን ከድርጅቱ የተቀበሉት የኦሮሚያ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ቶለሳ ገደፋ ድርጅቱ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው የተደረገው ድጋፍ በቅርቡ ከቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ ጋር በመሆን ለህብረተሰቡ እንደሚደርስ መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙዩኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡