ጃፓን ለኢትዮጵያ 5 ሺሕ 700 ሜትሪክ ቶን ሩዝ ድጋፍ አደረገች

ግንቦት 9/2015 (ዋልታ) የጃፓን መንግስት ለኢትዮጵያ 5 ሺሕ 700 ሜትሪክ ቶን ሩዝ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ፡፡

ድጋፉ በኢትዮጵያ እና በጃፓን መንግስት መካከል ቀደም ሲል የተፈረመ የድጋፍ ስምምነት ሲሆን በዛሬው ዕለት ርክክብ መደረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

የሩዝ ድጋፉ በገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ መካከል ርክክብ ተደርጓል፡፡

ድጋፉ በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት እና እየጨመረ የመጣውን የሩዝ ምርት ፍላጎት ለማስተካከል አስተዋፅዖ ያደርጋልም ነው የተባለው፡፡

የተደረገው ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን 300 ሚሊየን ብር እንደሚያወጣም ተጠቅሷል።