የሐላላ ኬላ ሪዞርት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በይፋ ተረከበ

ግንቦት 24/2015 (ዋልታ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ’ገበታ ለ ሀገር’ ፕሮጀክት አካል የሆነው እና በኮይሻ ፕሮጀክት ክላስተር ሥር የለማውን የሐላላ ኬላ ሪዞርት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ዛሬ በይፋ መረከቡ ተገለጸ።

ሪዞርቱን ‘ሐላላ ኬላ ሪዞርት’ በሚል ስያሜ ለማስተዳደር የክልሉ መንግሥት ከፓራዳይዝ ሎጆች፣ ሪዞርቶች እና ሆቴሎች ማኔጅመንት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ጋር ስምምነት ማድረጉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡