ከ2015 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ያለፉት 3 ነጥብ 2 በመቶ ብቻ ናቸው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

መስከረም 28/2016 (አዲስ ዋልታ) ከ2015 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ያለፉት 3 ነጥብ 2 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ።

የዘንድሮው ፈተና በጥቅሉ በ2014 ዓመት ከነበረው ከፍተኛ ለውጥ የታየበትና ከኩረጃና ሌብነት የጸዳ እንደነበር ገልጸዋል።

በአጠቃላይ በ2015 ከተፈተኑ ተማሪዎች ውስጥ ያለፉት 50 በመቶ ውጤት በማምጣት ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚያስገባ ውጤት ያመጡት 27 ሺሕ 267 ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ይህም ከአጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ የማለፊያ ነጥብ ያመጡት 3 ነጥብ 2 በመቶ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።

የዘንድሮው ከፍተኛ ውጤት በተፈጥሮ ሳይንስ 649 ከ700 በማምጣት መመዝገቡን አንስተው በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 533 ከ600 ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።

ከተፈጥር ሳይንስ ተፈታኞች ውጥስ 205 ተማሪዎች ከ600 በላይ ውጤት ሲያስመዘግቡ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 15 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት ማምጣታቸውን መናገራቸውን የኢዜአ ዘገባ አመላክቷል።