አደንዛዥ ዕፅ እና ዕለተዊ መጤ ልማዶች በታዳጊዎች እና ወጣቶች ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ተገለጸ

 

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)

ግንቦት 19/2016(አዲስ ዋልታ) አደንዛዥ ዕፅ እና ዕለተዊ መጤ ልማዶች በታዳጊዎች እና ወጣቶች ላይ ዘርፈ ብዙ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ተገለጸ።

አደንዛዥ እና እለታዊ መጤ ልማዶች በታዳጊዎች እና ወጣቶች ስብዕና ላይ የሚያሳድሩትን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመከላከል የተሰሩ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል።

በአፈጻጸም ግምገማው ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) አደንዛዥ እና እለታዊ መጤ ልማዶች የወጣትነትን መንፈስ የሚቀማና እንደ ሀገር አምራች ዜጋን በማሳጣት ለኪሳራ የሚዳርግ በመሆኑ ሁሉም ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚያዝያ 2015 እስከ ሚያዚያ 2016 ዓ.ም በርካታ የፖሊሲና መመሪያ ማሻሻያዎችን አና ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሠራታቸውን ተናግረዋል፡፡

በራሳቸው ባህል እና ታሪክ የሚኮሩ ወጣቶችን ለመፍጠር ትምሀርት ቤቶች፣ወላጆች ፣የሀይማኖት አባቶች እና የሚመለከታቸው አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባልም ብለዋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ሙና አህመድ ባቀረቡት ሪፖርት 12 ሺሕ 962 በላይ ሺሻ መጠመቀሚያ ዕቃዎች እና 70 ኪሎ ግራም አደንዛዥ እፅ መወገዱን ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ በ7 መቶ 38 የሺሻ እና ጫት ንግድ ቤቶች መዘጋታቸውንና አና በህገ- ወጥ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ 3 ሺህ 241 የስፖርት ውርርድ (sport Betting) ቤቶች ላይም እርምጃ ተወስዷል ብለዋል ።

በብርቱካን መልካሙ