ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከማርዮት ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንትና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጋር ተወያዩ

ሰኔ 26/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት የማርዮት ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አንቶኒ ካፑአኖ ጋር ተገናኝተው በማደግ ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ የጉዞ እና የሆስፒታሊቲ ዘርፍ ላይ ተወያይተዋል።

በውይይቱም በባህል ሀብቷ እና ታሪካዊ ቅርስ ይዞታዋ ብሎም በአስደናቂ የመልክዓ ምድር ገፅታዋ የታወቀችው ኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢንዱስትሪዋን በማስፋፋት ላይ ማተኮሯ ተገልጿል።

በዓለም ዙሪያ 8785 ያህል ቅርንጫፎች እና የሀብት አድራሻዎች በመያዝ በመስተንግዶ እና ማረፊያ አገልግሎት ዘርፍ መሪ የሆነው ማሪዮት ኢንተርናሽናል በዚህ ስራ ጉልህ ሚና ለመጫወት ትልም መያዙንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።