አዲስ ዋልታ በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ያመጣቸው የተቋም ማሻሻያ ስራዎቹ መማርያ ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው – የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ቢሮ ኃላፊ

ሰኔ 28/2016 (አዲስ ዋልታ) አዲስ ዋልታ በተቋም ማሻሻያዎቹ ያመጣቸው የለውጥ ስራዎች ለሌሎች ተቋማት መማርያ ሊሆኑ የሚችሉ መሆናቸውን የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈ ቤት የአደረጃጀት ቢሮ ኃላፊ ነቢዩ ስሁል ገለጹ።

ኃላፊውን ጨምሮ በርካታ የብልፅግና ፓርቲ አባላት አዲስ ዋልታ ኤፍ ኤም 105.3 እና የአዲስ ዋልታ ቴለቪዥንን ጎብኝተዋል።

አዲስ ዋልታ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ያመጣቸው አዳዲስ የሆኑ የዝግጅት አቀራረቦች መሰረታቸውን ተመልካቾቹ ላይ በማድረጉ ተቋሙ በበርካቶች ዘንድ እንዲወደድ አድርጎታል ሲሉ በጉብኝቱ የተሳተፉ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ተናግረዋል።

ለሰራተኞች ምቹ ከባቢን በመፍጠር እንደ ሀገር የተያዘውን እቅድ እየተገበረ ያለ ጠንካራ ተቋም ሆኖ አግኝተነዋል ያሉት የብልፅግና ፓርቲ አመራር እና አባላት ሌሎች ተቋማትም ልምድ መውሰድ ይገባቸዋል ብለዋል።

ሚዲያ ለሀገር ግንባታ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ የመገናኛ ብዙኃን ለህዝብ የሚቀርቡ ስራዎችን በመስራት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።

በግዛቸው ይገረሙ