የኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች ስብሰባ ተካሄደ


ሰኔ 28/2016 (አዲስ ዋልታ) የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች ስብሰባ ተካሄደ።

የውጭ ጉዳይ ዴኤታ አምሳደር ምስጋኑ አረጋ ስብሰባው በሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢ የሚከሰቱ ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች እልባት ለመስጠት በር የሚከፍት ነው ብለዋል።

ለአብነትም በዜጎች ላይ የሚከሰተውን ህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የህጻናት አፈናና እንደንብረት ውደመት ያሉ ጉዳዮችን የሚቀንስ መሆኑን ተናግረዋል።

የሁለቱ ሀገራት መንግስታት የጋራ ባህልና እሴት ያላቸውን የድንበር አካባቢ ህዝቦች የሚያገናኝ መሠረተ ልማት ለመገንባት በትብብር እንደሚሰራም ገልፀዋል።

የደቡብ ሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ሜንደይ ሰመያ ኩምባ ስብሰባው ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በታሪካቸው ወርቃማ የሆነውን የጋራ ትስስር የሚፈጥሩበት መሆኑን ገልጸዋል።

በ2011 የጀመረው የሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነትን ደቡብ ሱዳን አጠናክራ እንደምትቀጥልም ጠቁመዋል።

በኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካኝነት ለሁለት ቀናት በተካሄደው ስብሰባ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ፍስሃ ሻውል፣ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል መሃዲ እና የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ልዑክ ተገኝተዋል።

በሰማኸኝ ንጋቱ