አየር መንገዱ ከኮምቦልቻ ወደ ባህር ዳር ቀጥታ በረራ ሊጀመር ነው


ሐምሌ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) ከኮምቦልቻ ወደ ባህር ዳር ከተማ ቀጥታ በረራ ሊጀመር መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።

በአየር መንገዱ የኮምቦልቻ ኤርፖርት ኦፕሬሽን ኃላፊ ሰለሞን አበበ እንደገለጹት ከከምቦልቻ ወደ ባህር ዳር እና ከባህር ዳር ወደ ኮምቦልቻ የነበረው በረራ ተቋርጦ ቆይቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት መንገደኞች በተደጋጋሚ በረራው ዳግም እንዲጀመር በመጠየቃቸው አየር መንገዱ ከሐምሌ 13 ቀን 2016 ጀምሮ በየቀኑ መብረር እንደሚጀምር ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ተገልጋዮች ከሐምሌ 13 ቀን 2016 ጀምሮ ቀጥታ ከኮምቦልቻ ባህር ዳርና ከባህር ዳር ኮምቦልቻ መጓዝ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡