ከ237 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ተኪ ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ ቀረበ


ሐምሌ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት ከ237 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተኪ ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ መቅረቡን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

ኮርፖሬሽኑ የ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸሙን በሀዋሳ ከተማ እየገመገመ ሲሆን ተቋሙ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ከ606 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን ማምረት መቻሉ ተገልጿል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት ከተመረቱት ተኪ ምርቶች ውስጥ የቢራ ገብስ ብቅልና የኮንስትራክሽን እቃዎች ግብዓት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በተለይ የቢራ ፋብሪካዎች በግብዓትነት የሚጠቀሙትን የቢራ ገብስ ብቅል ሙሉ ለሙሉ መተካት መቻሉ ተመላክቷል፡፡

በእቅድ አፈጻጸም ግምገማው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚመረቱ ምርቶችን ለሀገር ውስጥ አምራቾች ለማቅረብ ከ124 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ግብዓቶችን ለአምራቾች በማቅረብ የገበያ ትስስር ስለመፈጠሩ ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡