ኢትዮጵያዊው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ አፍሪካዊ ስፖርተኛ ተባለ

ኢኤስፒኤን (ESPN) የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ 10 ታላላቅ አፍሪካውያን ስፖርተኞችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ እና ኬኒያ ሁለት አትሌቶችን በማስመረጥ ቀዳሚውን ደረጃ ይዘዋል።

ኢትዮጵያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ቀዳሚውን ደረጃ ሲይዝ ኬንያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ ኤሉድ ኪፕቾጌ ሁለተኛ እንዲሁም ካሜሮናዊው የእግር ኳስ ጥበበኛ ሳሞኤል ኤቶ ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በሴቶች የዚምቧብዌዋ የዋና ስፖርት ተወዳዳሪ ክርስቲ ኮቨንትሪ ቀዳሚውን ደርጃ ስትይዝ ኢትዮጵያዊቷ የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በሴቶች ሁለተኛ በሁለቱም ጾታ ደግሞ አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላለች።

አይቮሪኮስታዊው ዲድየር ድሮግባ፣ ኬኒያዊቷ ፌዝ ኪፕዬጎን፣ ደቡብ አፍሪካዊው ጃኩዌስ ካሊስ፣ ናይጀሪያዊቷ አሲሳት ኦሽዋላ እንዲሁም ግብጻዊው ሞሃመድ ሳላህ ከስድስተኛ እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።