በጥቁርና ነጭ ገበያው መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ በማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራው ለማሳካት የታሰበ ነው – የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ

ነሐሴ 1/2016 (አዲስ ዋልታ) በጥቁርና ነጭ ገበያው መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ በማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራው ለማሳካት የታሰበ ነው ሲሉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ገለጹ።

በዛሬው ዕለት በተካሄደው 27 ባንኮች የተሳተፉበት የልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር 107.9 ብር እንደተሸጠ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በጥቁር እና ነጭ ገበያው መካከል ያለው ልዩነት መጥበብ እና የምንዛሪ ተመን መረጋጋት በአንድ ሳምንት ውስጥ ልዩነት ማሳየቱን ገልጸው ኢትዮጵያ በጀመረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራ ለማሳካት የታሰበውም ይህ ነው ብለዋል።

የዛሬው አማካይ ዋጋ የነገ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጠቋሚ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ እንደሆነ ባንኩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።