በአፍሪካ ተወዳዳሪ ሊሆን የሚችል ሚዲያ እየገነባን ነው – መሐመድ ሀሰን

ነሐሴ 20/2016 (አዲስ ዋልታ) ያሉንን መልካም እሴቶች ይዘን አዳዲስ ሀሳቦችን በማምጣት ከኢትዮጵያም ባለፈ በአፍሪካ ተወዳዳሪ ሊሆን የሚችል ሚዲያ እየገነባን ነው ሲሉ የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈፃሚ መሐመድ ሀሰን ተናገሩ።

ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ከተባባሪ አካላት ጋር በጋራ መስራት በሚችልባቸው ጉዳዩች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው ተቋሙ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ተጨባጭ የሪፎርም ለውጦች ማድረጉን ጠቅሰው በዚህም ተመራጭ ሚዲያ ለመሆን መብቃቱን ተናግረዋል።

አያይዘውም ተቋሙ በሚዲያው ኢንዱስትሪ ውስጥ ለዘመናት የቆየና የራሱን አሻራ ያሳረፈ መሆኑን አንስተዋል።

የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈፃሚ መሐመድ ሀሰን

ተባባሪ አካላት በበኩላቸው በተቋሙ የተመለከቱት ለውጦች አዲስ ዋልታ እራሱን ግዙፍና ተመራጭ ሚዲያ ለማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን እንደሚያሳይ ገልጸው በጋራ ለመስራት የተደረገው ውይይትም ጥሩ ነው ብለዋል፡።

አሁን ላይ የማኅበራዊ ሚዲያው ተጽዕኖ ከፍ እያለ መምጣቱን የጠቀሱት ተባባሪ አካላቱ አዲስ ዋልታ በዚህ ላይ የሚሰራውን ሥራ አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ከብራንዲግ ጀምሮ አዳዲስ ለውጦችን በማድረግ ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ መድረሱ የሚታወስ ነው።

በሳራ ስዩም