መስከረም 11/2017(አዲስ ዋልታ) በካዛንቺስ፣ አዋሬ እና ቤተመንግስት ዙሪያ በኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት እስካሁን 674 በቀበሌ ቤት የሚኖሩ የልማት ተነሺዎች የተለዋጭ መኖሪያ ቤት ዕጣ አውጥተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቀበሌ ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች በተገነቡ ዘመናዊ የመኖሪያ ህንጻዎች ተለዋጭ ዘመናዊ የቀበሌ ቤቶችን በፍትሃዊነት በእጣ እንዲያገኙ እያደረገ ይገኛል።
በዚህም እስካሁን 674 በቀበሌ ቤት የሚኖሩ የልማት ተነሺዎች የተለዋጭ መኖሪያ ቤት ዕጣ ያወጡ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 90 የአካል ጉዳተኞች መኖራቸው ተገልጿል።
ከአካባቢዎቹ እስካሁን 1ሺሕ 218 የቀበሌ ቤቶች መረጃቸው ተጣርቶ የተደራጁ ሲሆን እጣ የማውጣት ሂደቱም በቀጣይ ቀናት እንደሚቀጥል የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።
የልማት ተነሺዎች በሂደቱ ቅሬታ ካላቸው የሚያቀርቡበት ስርዓትም በየደረጃው መዘርጋቱ ተጠቁሟል።