ጥቅምት 14/2017 (አዲስ ዋልታ) በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 525 ንዑስ አንቀፅ 1(ለ) ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ በአደገኛ ዕፅ ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ የተለያዩ ሀገራት ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ከ2 ዓመት እስከ 12 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት መቀጣታቸው ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ እንዳስታወቀው፤ በ2016 በጀት ዓመት በዕፅ ዝውውር ከደረሱ ጥቆማዎች መካከል ጠቅላይ መምሪያው የምርመራ መዝገቦችን በሰውና በሰነድ አጣርቶ ለዓቃቤ ሕግ ከላከው መዝገቦች ውስጥ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ናቸው ብሎ ውሳኔ ያስተላለፈባቸው ግለሰቦች፡-
1. ሚ/ር ቺቡኬ ዳንኤል 12 ዓመት ፅኑ አስራት እና 4,000 ብር መቀጮ፣
2. ሚ/ር ኢጎር ዲማቶስ ዱትራ 3 ዓመት ከ9 ወር ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
3. ሚ/ር ሉዊስ ሚጎል ኮናሮጂ 4 ዓመት ፅኑ አስራት እና 4,000 ብር መቀጮ ፣
4. ሚ/ር ኬብሮም ሙንዲሀኪ 4 ዓመት ፅኑ አስራት እና 2,000 ብር መቀጮ፣
5. ሚ/ር ሳንጀብ ሙክርጂ 6 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ አስራት እና 7,000 ብርመቀጮ፣
6. ሚ/ር ሚስ ጊርሊዬ አሚ 3 ዓመት ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
7. ሚስ ሄልቪ አልቫላ 5 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ አስራት እና 5,000 ብር መቀጮ፣
8. ራሄል ለገሰ 3 ዓመት ፅኑ አስራት 3,000ብር መቀጮ፣
9. ተስፋነሽ አለንሳ 3 ዓመት ብር ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ ፣
10. ሚስስ ፑርናማ ጊታ 15 ዓመት ብር ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
11. ሚስ ናፈትፓት ኑአመንሮም 4 ዓመት ከ 5 ወር ፅኑ አስራት እና 5,000 ብር መቀጮ፣
12. ሚስ ዚቱየትነህ 5 ዓመት ፅኑ አስራት እና በብር 3,000 ብር መቀጮ፣
13. ሚ/ር ማርክ ፖወሊኮወ 5 ዓመት ከ 6 ወር ፅኑ አስራት እና 5,000 ብር መቀጮ፣
14. ሚ/ር ኢማኑኤል ኡዙቸክው 6 ዓመት ፅኑ አስራት እና 8,000 ብር መቀጮ፣
15. ባህሩ ወልዴ 12 ዓመት ፅኑ አስራት፣
16. ሚ/ር አስዋልደረፋይል ሄርና 4 ዓመት ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ ፣
17. ታምሩ ፍቅሬ 12 ዓመት ፅኑ አስራት እና 4,0000 ብር መቀጮ፣
18. ግሬስ አዋርድር 2 ዓመት ከ9 ወር ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
19. ሚስ ዜመዬ አዩን 5 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
20. ሚ/ር ሞሀመድ ሳሉሞኪላማ 6 ዓመት ፅኑ አስራት እና 5,000 ብር መቀጮ፣
21. ሚ/ር ሩአንደርሰደ ሰመዝ 3 ዓመት እስራት ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
22. ሚ/ር አሊዬ አቡዋ 4 ዓመት ፅኑ አስራት እና 2000 ብር መቀጮ፣
23. ሚስ ቻኒካን ቡናሙኤን 3 ዓመት ፅኑ አስራት እና 3,000 ብር መቀጮ፣
24. ሚስስ ቱርናማ ጊታ ሳሪ 4 ዓመት ፅኑ አስራት እና 5,000 ብር መቀጮ ናቸው።
የተያዙ ኢግዚቢቶች በአይነት እና በመጠን በአጠቃላይ 176,881.61ግራ ምኮኬን፣ 924,450 ግራም ካናቢስ፣ 32,100.89 ግራም ሄሮይን፣ 5,089 ግራም ሄሮይን እና ሞርፊም መሆናቸው ታውቋል።
ግለሰቦቹ ዕፁን ለማዘዋወር የሚጠቀሙባቸው መንገዶች በሰው አካል ውስጥን ጨምሮ በሻንጣ ውስጥ፣ በጫማ ሶል፣ ወፍራም ልብስ በማስመሰል በመልበስ፣ በተለያየ የመኪና አካል ውስጥ፣ በሻንጣ መጎተቻ ብረት ውስጥ በመበየድ እና በሌሎችም መንገዶች እንደሆነ የወንጀል ምርመራ ቡድኑ አረጋግጧል።
የዕፅ የአዘዋዋሪዎቹ ሀገራት:- ናይጀሪያ፣ ኢትዮጵ፣ ብራዚል፣ ታይላንድ፣ አንጎላ፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቪንዙዌላ፣ ቤኒን፣ ካሜሮን፣ ናሚቢያ፣ ኮንጎ፣ ኡጋንዳ፣ ኬኒያ፣ ቦሊቪያ፣ ፖላንድ፣ ጀርመን፣ ሴንትራል አፍሪካ፣ ህንድ፣ ቱኒዚያ፣ ኢንዶኒዥያ፣ ማላዊ፣ ጅቡቲ፣ ካናዳ፣ ሞዛምቢክ እና ተርክዬ መሆኑ ታውቋል።
የአደገኛ ዕፅ አዘዋወሪዎቹ መነሻ ብራዚል (ሳኦፖውሎ)፣ ደቡብ አፍሪካ (ጆሃንስበርግ)፣አዲስ አበባ፣አንጎላ ታንዛኒያ፣ ኬኒያ እና ሌሎች ሀገራት ሲሆን መዳረሻቸው ደግሞ ናይጀሪያ (ሌጎስ)፣ ደቡብ አፍሪካ (ጆሃንስበርግ)፣ ህንድ፣ ዱባይ እና ታይላንድ መሆናቸው ተጠቅሷል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ችሎት 24 የምርመራ መዝገቦችን መርምሮ በሕግ የተከለከሉ ዕጾችን የማዘዋወር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾችን ያርማል፤ ሌሎችን ያስተምራል በማለት ከ2 ዓመት እስከ 12 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲሁም ከ2 ሺህ ብር እስከ 8 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ወስኖባቸዋል።
በተመሳሳይ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር በዋሉት ላይም ምርመራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።