ጥቅምት 14/2017 (አዲስ ዋልታ) የተባበሩት መንግስታት ቀን በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተከበረ።
የተባበሩት መንግስታት ቀን ድርጅቱ እ.ኤ.አ 1971 ባሳለፈው የውሳኔ ሀሳብ ቁጥር 2782 መሰረት በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በየዓመቱ ጥቅምት 24 ይከበራል።እለቱ እ.ኤ.አ 1945 የተቋቋመውን የተባበሩት መንግስታት ምስረታ በማሰብ የሚከበር
ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት የድርጅትን እሴቶችና አላማዎች በሚያስተዋውቁ ዝግጅቶች እና ተግባራት ይከበራል።እለቱ ሲከበር የዓለም ሰላም፣ የሰብአዊ መብቶች፣ የአየር ንብረት ለውጥን የመከላከል እርምጃዎች እና ሌሎች ጉዳዮችን በማንሳት ለመፍትሄው በጋራ ለመስራት በመዘጋጀት እንደሆነ ታውቋል።
በዓለም አቀፍ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት በማድረግና በመተባበር የድርጅቱን ቻርተር አላማ በጋራ ለማሳካት ይሆናል መባሉንም ኢዜአ ዘግቧል።