በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ጥቅምት 14/2017 (አዲስ ዋልታ) አንድ ደላላ እና ሁለት ፈፃሚዎች በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ሰልፍ በመያዝ እና ተገልጋይ በመመዝገብ ገንዘብ የሚሰበስብ በፓርኪንግ ስራ ላይ የተሰማራ ህገ-ወጥ ደላላ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ከደላላው ጋር ተመሳጥሮ በሌብነት ላይ የተሰማራ አንድ የንግድ ቢሮ የወረዳ ጽ/ቤት ሰራተኛ እንዲሁም የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ሰራተኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
ለከተማ አሰተዳደሩ ከነዋሪ በደረሰ ጥቆማ መነሻ የኤጀንሲው ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በሰራው ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።