ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በሊባኖስ እና ፍልስጤም የሚደርስው ውድመት እንዲቆም ጠየቁ

ጥቅምት 14/2017 (አዲስ ዋልታ) የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በሊባኖስ እና ፍልስጤም እየደረሰ ያለው ውድመት እንዲቆም ጠየቁ።
ፕሬዝዳንቱ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርሶ “የሁለት አገርነት” መርህ እንደመፍትሄ እንዲሰራበት ከመጠየቃቸው በተጨማሪ በሊባኖስ በመስፋፋት ላይ ያለውን ጦርነት እንዲቆም በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።
በሊባኖስ እና ፍልስጤም ከዚህ በላይ ጥፋት እና ስቃይ ሊኖር አይገባም ሲሉም መናገራቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።
በጋራ በመሆንም ለሰላም የቆመ ኃይል መመስረት እንደሚገባ እና የግጭቶቹን መሰረታዊ ምክንያቶች ለመቅረፍ የሚያስችል መፍትሄ ማምጣት ይገባል ሲሉ በሩሲያዋ ካዛን ባደረጉት ንግግር ጥሪ አቅርበዋል።
በዚሁ የብሪክስ ጉባዔ ላይ የኢራኑ ፕሬዝዳንት መስኡድ ፔዚሽኪያን የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤትን በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣውን ግጭት ማስቆም ባለመቻሉ ተችተዋል።