ከሊባኖስ 125 ኢትዮጵያዊያን ተመለሱ

ጥቅምት 18/2017 (አዲስ ዋልታ) በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 125 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
በዚሁ መሠረት በትናንትው ዕለት 61 እና በዛሬ ዕለት ደግሞ 65 ዜጎች ከሊባኖስ እንዲመለሱ መደረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቤይሩት ከሚገኘው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ጋር በመሆን በቀጣይም ሌሎች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ አስፈላጊውን ጥረት እያደረገ ይገኛልም ተብሏል።