የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት ባለፉት 13 ዓመታት በአራት ክልሎች ከ 5ሺ በላይ የሚሆኑ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማትን ማስገንባቱን የፌደራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚንስቴር አስታወቀ ።
በሚኒስቴሩ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ሰኢድ ኡመር ለዋልታ እንደገለጹት በአገሪቱ የአርብቶ አደር አካባቢ ተመጣጣኝ ልማት ለማምጣት ከ1996 ዓም ጀምሮ የአፋር ፣ ሶማሌ ፣ኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች በአርብቶ አደር ማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት አማካኝነት የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት የሚሠጡ ተቋማት ሲገነቡ ቆይተዋል ።
ፕሮጀክቱ አብርቶ አደር በሚበዛባቸው ክልሎች ተግባራዊ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሰኢድ ባለፉት 13 ዓመታት በ112 ወረዳዎች የትምህርት ፣ የመጠጥ ውሃ ፣ የመንገድ ፣ የአርብቶ አደር ማሠልጠኛና የሰውና የእንስሳት የጤና ተቋማት መገንባታቸውን ተናግረዋል ።
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ብቻ ፕሮጀክቱ 774 ያህል የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማትን ለማስገንባት በዕቅድ ይዞ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሰኢድ 653 የሚሆኑት በፕሮጀክቱ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቀው ለአርብቶ አደሩ አገልግሎት መሥጠት ጀምረዋል ብለዋል ።
ፕሮጀክቱ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተግባራዊ ከማድረጉ በፊት የአካባቢውን አርብቶ አደሩን ያወያያል ያሉት አቶ ሰኢድ ማህበረሰቡ ቅድሚያ ለሚሠጠውና ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማት ግንባታ እንደሚከናወን ገልጸዋል ።
በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ከተጀመረ አንስቶ በሦስት ምዕራፎች 1ነጥብ 4 ሚሊዮን የሚሆኑ አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረጉን የገለጹት ሰኢድ እስካሁን ከ 400 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ ተደርጓል ።
የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ፕሮጀክት ከፊሉን ወጪ የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግሥት ሲሆን የዓለም አቀፉ ልማት ማህበር( አይዲኤ) እና ዓለም አቀፉ የምግብና የእርሻ ልማት ( ኢፋድ) በተገኘ ድጋፍ እየተካሄደ ይገኛል ።
የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት ባለፉት 13 ዓመታት በአራት ክልሎች ከ 5ሺ በላይ የሚሆኑ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማትን ማስገንባቱን የፌደራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚንስቴር አስታወቀ ።
በሚኒስቴሩ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ሰኢድ ኡመር ለዋልታ እንደገለጹት በአገሪቱ የአርብቶ አደር አካባቢ ተመጣጣኝ ልማት ለማምጣት ከ1996 ዓም ጀምሮ የአፋር ፣ ሶማሌ ፣ኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች በአርብቶ አደር ማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት አማካኝነት የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት የሚሠጡ ተቋማት ሲገነቡ ቆይተዋል ።
ፕሮጀክቱ አብርቶ አደር በሚበዛባቸው ክልሎች ተግባራዊ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሰኢድ ባለፉት 13 ዓመታት በ55 ወረዳዎች የትምህርት ፣ የመጠጥ ውሃ ፣ የመንገድ ፣ የአርብቶ አደር ማሠልጠኛና የሰውና የእንስሳት የጤና ተቋማት መገንባታቸውን ተናግረዋል ።