ዘንድሮ ከማኑፋክቸሪንግ ምርቶች ዘርፍ ከ913 ነጥብ 6 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ለማግኘት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
የሚኒስቴሩ የውጪ ንግድ ማስፋፊያ ዳሬክቶሬት ጀነራል ዳይሬክተር አቶ አሰፋ ሙሉጌታ ለዋልታ እንደገለጹት፤የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን በማስፋት ወደ ውጭ ከሚላከው ምርት የሚገኘው ገቢ በሶስት እጥፍ ለማሳደግ እየሰሩ ይገኛሉ ፡፡
ማንፈከቸሪንግ ምርቶቹ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ጨርቃጨርቅና አልባሳት ፣ምግብ መጠጥና ፋርማሲቲካል ፣ኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብአቶች፣ ስጋና ወተት ተዋጽኦዎች ፣ብረታብረት ፣ስኳርና ሞላሰስ መሆናቸውን ጠቁመዋል ፡፡
ከነዚህም ውስጥ ቆዳና ቆዳ ውጤቶች፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ምግብ መጠጥና ፋርማሲቲካል፣ ስጋና ወተት ተዋጽኦዎች እሴት የሚጨመርባቸው ናቸው ብለዋል፡፡
ስለሆነም የተሻለ ገቢ ለማግኘት ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ጥራትን ማሻሻል ተሳቢ መደረጉን ገልጸዋል ፡፡
እንደዚሁም ዘመናዊ የግብይት ስርዓትን ማስፋት እና የተሳለጠ በማድረግ በሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በአሰራር እየተመለሱ እንደሚሄዱ አብራርተዋል ፡፡
በተለይም የኢንዳስትሪው ፓርኮቹን እንደ አንድ ግብኣት በመጠቀም በተሻለ በደገፍና በጠናከር መስራት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል ፡፡
በተለይም ህገ ወጥ ንግዱን በተለየ መልኩ የመከላከልና አቅርቦቱን ማሻሻል ላይ ስራ ይካሄዳል ብለዋል ፡፡
ዘርፉን ቀልጣፋ ለማድረግ የሎጂስቲከስ የጉሙሩክ አሰራሮችን የበለጠ በመቃኘት በቅንጅት መስራት መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡
በለፈው ዓመት ከማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ከ300 ሚሊየን ዶላር በላይ መገኘቱን ለማወቅ ተችሏል ፡፡