የባቡር ፕሮጀክቱ የአገሪቱን የትራንስፖርት ዘርፍ ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል- የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚነስትር

ከአዲስ አበባ ጁቡቲ የተገነባው ዘመናዊ የባቡር መስመር ዛሬ በአዲስ አበባ ፉሪ ለቡ ጣቢያ በኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እና በጁቡቲ ፕረዚደንት እስማዒል ዑመር ጌለ ተመርቌል ።

የኢትዮጵያ ከጁቡቲ የሚያገናኘው 758 ኪሎ ሜትር መስመር የመረቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ባሰሙት ንግግር መስመሩ የአገራችን ኢኮኖሚ ዕድገትና ህዳሴዋን ለማስቀጠል እንዲሁም መዋቅራዊ ሽግግርን ለማፋጠን ድህነትን ለመቀነስ የሚኖሮው ሀገራዊ ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል።  ፣

በ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ወጪ የተገነባው የባቡር መስመሩ ሙሉ  በሙሉ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ በመሆኑ በአፍሪካ ምድር የመጀመሪያው ረጅም ርቀት የባቡር መስመር ተብሎ የሚወሰድ ነው ብለዋል።

በተመሳሳይ መንገድ የኢትዮጵያ የጁቡቲ በአጠቃላይም ምስራቅ አፍሪካ የሚያገናኝ ታሪካዊ መስመር መሆኑን አመልክተዋል ።

ይህ መስመር ከዚህ ቀደም በተሽከርካሪ ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ ለመሄድ ከ 4ቀናት በላይ ይወስድ የነበረው የአገሪቱ የወጭና የገቢ ምርቶች በአንድ ቀን ውስጥ በዝቅተኛ ወጭ ማጔጔዝ የሚያስችል በመሆኑ አገራችን በዓለም ገበያ ላይ የሚኖራትን ተወዳዳሪነት የሚያሳድግ መሆኑን አስረድተዋል ።

ፕሮጀክቱ አገራችን የተያያዘችውን የኢንዳስትሪ ዕድገት ለማፋጠን የሚኖሮው አገራዊ ፋይዳ ጉሉህ መሆኑን አስታውቀዋል።

የምድር ባቡር አዳማ-ድሬዳዋ- ደወሌ  እና ሌሎችም  ከተሞች  የቀድሞ ጥንካሬያቸውን እንደገና አድሰው በፈጣን ዕድገት ወደፊት እንዲጔዙ ብሩህ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል ብለዋል ።

የአገራችን ህዳሴ ቀጥሎ በሌሎች አከባቢዎችም ዘመናዊ የባቡር አገልግሎቱ የሚስፋፋበት ሁኔታ ሩቅ እንደማይሆን አረጋግጠዋል።

በመስመሩ የሚገነቡት የኢንዳስትሪ ፓርኮችና ዘመናዊ የግብርና ምርቶች የዜጎችን የስራ ዕድል የሚፈጥሩ ከመሆናቸውም በላይ አገራችን የተያያዘችውን ፈጣን ኢኮኖሚ በማስቀጠል እ ኤ አ በ2025 መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለማሰለፍ የምታደርገውን ጥረት የሚያሳካ መሆኑን ገልጸዋል።

የፕሮጀክቱ ልዩ ባህሪ በጁቡቲና በኢትዮጵያ ህዝቦች ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት የሚያበለጽግ ከመሆኑም በላይ የአገሮቹ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ትስሰር ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ ትልቅ ሚና ይኖሮዋል።

የጁቡቲ ፕረዚዳንት እስማዒል ዑመር ጌለ በበኩላቸው ከፍተኛ በጀት የፈሰሰበት የባቡር መስመሩ የሁለቱ አገሮች ህዝቦች ንብረት ስለሆነ በመስመሩ የሚኖሮው ህዝቦች መጠበቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል ።

በምርቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የቶጎ ፕረዚደንት ማዘምቤና የቻይና መንግስት ተወካይ ዙ ሾሺ ጨምሮ በርካታ የመንግስት ባለስልጣናትና የአዲስ አበባ ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው ዕንግዶች የተገኙ ሲሆን ባቡሩም በይፋ የሙኮራ ስራውን መጀመሩን ዋልታ ዘግቧል።