ልማት ባንኩ ለኢትዮጵያ ኩባንያዎች 60 ሚሊየን ዶላር ብድር ፈቀደ

የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የንግድና ልማት ባንክ ለሶስት የኢትዮጵያ ኩባንያዎች 60 ሚሊየን ዶላር ብድር ፈቀደ፡፡

ብድሩ የተፈቀደው ለፑል ማን ሆቴሎች፣ ጋቴፕሮ የብረታብረት ኢንጂነሪንግና የአክሰር ሆቴሎች ግሩፕ ነው፡፡

እነዚህ ኩባንያዎች ለኢትዮጵያ ከፍተኛ  የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት በሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ብድሩ እንዲፈቀድላቸው ዓይነተኛ ምክንያት እንደሆነም ታውቋል፡፡

ብድሩ ሀገሪቱ በኃይል፣ ገንዘብ፣ ትራንስፖርት፣ ቱሪዝምና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎችን ለማገዝ የሚያስችል እንደሆነ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አድማሱ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

ባንኩ ቀደም ሲል በብሩንዲ እንደነበርና ሀገሪቱ ባላት አለመረጋጋት ቢሮውን ወደ ኬንያ እንደቀየረና ሁለተኛውን ቢሮውን ደግሞ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኢትዮጵያ እንደከፈተ ታውቋል፡፡

አቶ አድማሱ ባንኩን በፕሬዝዳንትነት መምራት ከጀመሩበት ጊዜ በኋላ ባንኩ በ300 በመቶ እድገት እነዳስመዘገበ ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ (www.ptabank.org)