በ200 ሚሊየን ዶላር የአርብቶ አደሩን ድርቅ ለመቋቋም ጥረት እየተደረገ ነው

የአርብቶ አደሩን የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ በ200 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ የተለያዩ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስትር ገለጸ

የአርብቶ አደሩን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስና የምግብ ዋስትናቸውን በዘላቂነት ለማረጋገጥ አገር አቀፍ በተዘጋጀው የ5 ዓመት ፕሮግራም ከ200 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ ተደርጎበት ድርቅን ለመቋቋምና ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚያስችል ስራሳዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን የሚኒስቴሩ ማህበረሰባዊ ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ ስዒድ ዑመር ገልጸዋል ፡፡

የፈረደራል መንግስት ባቋቋመው የልዩ ድጋፍ ቦርድ በምክርቤቱ የአርብቶ አደሩ ቋሚ ኮሚቴ ተደራጅቶ የክልሎችን ችግር ለመፍታት ድጋፍ እየተሰጠ እንደሚገኝ ነው የጠቀሱት  ፡፡

የኢትዮጵያ ሶማሌና የዓፋር ክልሎችም የደቡብና የኦሮሚያ ክልል የሚገኙ አርብቶ አደር የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውሃ  የእንስሳት ሃብት በማልማት ከገበያ ጋር በማስተሳሰር ተጠቃሚ ለማድረግ የውሃ ፣ትምህርትና የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ሽፋን በማሻሻል ረገድ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን አስረድተዋል  ፡፡

ባሁኑ ጊዜ የመጠጥ ውሃ ሽፋን በኦሮሚያ አርብቶ አደር 68 በመቶ ፣በዓፋር ክልል 63 በመቶ ፣  በኢትዮጵያ ሱማሌ 62 በመቶ እና በደቡብ 51 በመቶ መሆኑን ገልጸዋል  ፡፡

የመሰረታዊ ጤና ሽፋን በሱማሌ 88 በመቶ በዓፋር 89 በኦሮሚያ አርብቶ አዴሮች 78 እና የደቡብ 92 በመቶ ደርሷል ፡፡

የእንስሳት ጤና ሽፋን በተመለከተም በኦሮሚያ በ81 ፣በደቡብ አርብቶ አደር 72 በመቶ ፣በዓፋር 67 እና በኢትዮጵያ ሱማሌ 63 በመቶ  መድረሱንም እንዲሁ  ፡፡

የአንደኛ ደረጃ ትምህት ሽፋን በተለይም በኢትዮጵያ ሱማሌ 65 በመቶና በዓፋር 59 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል፡፡

በሚኒስቴሩ አስተባባሪነትና በአርብቶ አደሩ ክልሎች ከ1996 ዓም ጀምሮ የሚገኘው የአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ልማት ፕረጀክት በነዚህ ክልሎች የተጀመሩ የልማት የማህበራዊ አገልገሎት ስራዎች የራሱ ልማት ያለው ፕረጀክተ ይታወቃል ፡፡

የፕሮጀክቱ አንደኛና ሁለተኛ ምዕራፍ በማጠናቀቅ በሁኑ ጊዜ ወደ 3ኛ ምዕራፍ ተሸጋሮ በአፈጻም ላይ ይገኛሉ ፡፡

ይህ አርብቶ አደሩ ልማት ፕሮጀክት ባለፉት 13 ዓመታት 1ሺ 145 ወረዳዎች 430 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ 4ነጥብ5 ሚሊየን የአርብቶ አደሩ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ተጠቃሚና እያደረገ እና የገቢ ዓቅማቸውን እያሳደገ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል  ፡፡

ይሁን እንጂ ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት በተቀመጠው የአርብቶ አደር ልማት አቅጣጫ መሰረት ባለመፍታታቸው በዚህ ዓመትም የድርቅ ተጋላጭ በመሆናቸው መላው የአገሩ ህዝቦች የልማት አጋሮች የጋራ ርብርብ እንደሚጠይቅ ነው የተመለከተው ፡፡