ሰዎች ለሠዎች ድጋፉን ለኢትዮጵያ እንደሚቀጥል አስታወቀ

ሰዎች ለሰዎች የተባለዉ የጀርመኑ ምግባረ ሰናይ ድርጅት በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሚያካሂዳቸዉ የልማትና የአቅም ግንባታ ሥራዎች ወደ ሦስት መቶ ሚሊዮን የሚሆን የኢትዮጵያ ብር መመደቡን አስታወቀ።

 

የጀርመኑ ግብረሰናይ ድርጅት ድጋፉን ቀጥሎአል

 

ላለፉት 35 ዓመታት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ድጋፍን ሲያደርግ የኖረዉ የዚህ ድርጅት ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በድርጅቱ የተከሰተዉ አስቸጋሪ ሁኔታ ታልፎ ለጋሾች ለድርጅቱ የሚሰጡት የርዳታ መጠን በ 115 ከፍ ማለቱን አስታዉቀዋል። ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተገኘዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን አጠር ያለ ዘገባ ልኮልናል።  (www.dw.com)