አገራዊ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ከግብርና ወደ ኢንዳስትሪ መር በሚካሄደው ሽግግር ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት የንገድ ባንክ ዳይሬክተሬት ሰብሳቢ አቶ በረከት ስመዖን አስገነዘቡ ፡፡
መንግስት አገራዊ የካፒታል ክምችትን ለማጎልበትና ለኢንዱስትሪ ልማት የሚሆን ፋይናስ በተለይ ደግሞ የውጭ ምንዛሪ ለሟሟላት በልዩ ትኩረት ሲንቀሳቀስ መቆየቱን አቶ በረከት ስመዖን ገልጸዋል ፡፡
በአነስተኛ አርሶ አደር ማሳ ላይ በመስረት ለሩብ ምዕተ ዓመታት ያክል በተካሄደው ፈጣን ልማት አገራችን ወደ ኢንዳስትሪ ልማት ሊሰማራ የሚችል ፋይናንስ በሰፊው ለማቅረብም የምትችልበት ምቹ ሁኔታ በመፈጠር ላይ ነው ያሉት፡፡
ባለፉት በርካታ ዓመታት ላቁ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ልዩ በልዩ የመንግስትና የግል ትልልቅ ኢንቨስትመንቶችን ከራሳችን ውስጣዊ ምንጭ ለመሸፈን የሚያስችል ብቃት ማዳበራችን ለዚህ ዓይነተኛ ማረጋጫ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡
በተጨማሪም አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋይናንስና ልማትን እንደሚያገናኝ አንድ ድልድይ ቁጠባን የማሳደግ ስትራቴጂ ቀርጾ ይህንኑ ተግባረዊ ለማድረግ ከሀገራችን ህዝቦች ያሰባሰበው ተቀማጭ ገንዘብ 320 ቢልየን ብር መድረሱ ጨምረው አስረድተዋል፡፡
ባንኩ ከዓመት ወደ ዓመት በመጨመር ላይ ያለው የውጭ ምንዛሪ ግኝትም የልማታችን ፍሬና አገራዊ ልማታችን ጥረታችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያግዝ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን አመልክተዋል ፡፡
ይህም በሀገራዊ ፋይናስም ሆነ በውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ለደንኞች ፍላጎት ለማርካት የሚያደርገው ጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ የመጣ መሆኑን ገልጸዋል
ይሁን እንጂ የውጭ ምንዛሬ አቅርቦቱ እጅግ እያሻቀበ ከመጣው ፍላጎት ጋር ሊጣጣም ባለመቻሉ የደንበኞችን ታዳጊ ፍላጎት የሟሟላት ጉዳይ ራሱ የቻለ ተግዳሮት እንደሆነም ነው ያመለከቱት ፡፡
ባለፉት ዓመታት የአገራችን የውጭ ንግድ አፈጻጸም እንደሚያሳየው ለገበያ የምናቀርባቸው ምርቶች መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ቢሆንም ከነዚህ ጥሬ ምርቶች ሽያጭ የምናገኘው የውጭ ምንዛሬ መሆን የሚገባውን ያህል ጭማሪ አላሳየም ብለዋል ፡፡
ይህም እሴት ያልተጨመረባቸውን ምርቶች ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ በተነጻጻሪ እያነሰ ከመሄዱ ጋር የተቆራኘ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡
በመሆኑም የውጭ ምንዛሪ ግኝታቸውን ለማሳደግ በፋብሪካ እሴት የተጨመረባቸው ለገበያ ለማቅረብ መሸጋገር አጣዳፊ ሆኖ መገኘቱን አስገንዝበዋል ፡፡
አገራችን ያላት ተዳጊ የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ሊሟላ የሚችለው ደግሞ ኢኮኖሚያችን በኤክስፖርት ዘርፉ እየተመራ ከግብርና ወደ ኢንዳስትሪ መር ሲሸጋገርና ኢንዱስትሪውም በኤክሰፖርት ዘርፍ ሲመራ መሆኑን አስገንዝበዋል ፡፡
ስለሆነም አገራችን ወደ ውጪ ለምትለልካቸው ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር ይህንኑ በዓይነትና በመጠን በማጎልበት የውጭም ምንዛሬ አቅርቦትን አስተማማኝ ማድረግ ይገባል ዋልታ እንደዘገበው ፡፡