በሀገሪቱ ከ12ሺህ በላይ ገጠር ቀበሌዎች በመንገድ መገናኘታቸውን ባለስልጣኑ አስታወቀ

በመላ ሀገሪቱ ከ12 ሺህ በላይ ገጠር ቀበሌዎች በመንገድ መገናኘታቸውን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሰልጣን አስታወቀ ፡፡

የሁሉ አቀፍ መንገድ ተደራሽነት ፕሮግራም ከመጀመሩ በፊት ክረምት ከበጋ የሚያገለግል ከዋና መንገድ ጋር የተገናኙ መንገዶች ቀበሌዎች ብዛት 6 ሺህ 222 ብቻ የነበሩ ሲሆን፤ አሁን ላይ ግን ቁጥሩ ከ12 ሺህ በላይ መድረሱን የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ገልጸዋል ፡፡

ባሁኑ ወቅት በፕሮግራሙ ያልተገናኙ 3ሺ 600 ቀበሌዎች መኖራቸውን ጠቁመው፤ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋ|ል ፡፡

ለዚህም በአንዳንድ ክልሎች ተጀመርው ያልተጠናቀቁ ስራው እንዲፋጠን ይደረጋል ብለዋል ፡፡

በተጨማሪም የመንገድ ስራቸው ተጠናቀው  ከፕሮግራሙ ዓቅም በላይ ሆነው የቆዩት ከ እስከ  ሜተር ርዝመት ያላቸው ድልድየፖችን ዲዛይን ለማገባደድ ልዩ ድጋፍና ክትትትል እንደሚደረግም አመልክተዋል ፡፡

ባለስልጣኑ የመንገድ ልማቱን ለማዘመንንና ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ በለውጥ ሰራዊ ግንባታ ጭምር የመልካም አሰተዳር ችግሮች ነቅሶ በማውጣት የድርጊት መርሃ ግብር በማዘጋጀት ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡

በዚሁም መሰረት ከመንገድ ግንባና ጥገና ፣ከወሰን ማስከበር፣ ከካሳ ክፍያ ለተሽከርካሪዎች ክብደት ሚዛን ቁጥጥር እና የመንገድ ደህንነት ከማስጠበቅ አኳያ የሚታዩ የአስራር ግድፈቶች ለማስቀረት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡

እንደዚሁም የሚመለከተው የስራ  ኃላፊነት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን በድርጊት መርሃ ግብሩ መካተቱን ጠቁመዋል ፡፡

የመንገድ ተራቋጮችና አማካሪ ደርጅቶችን የአፈጻጸም ደረጃቸውን ለማወቅና ጠንካራውን ከደካማው ለመለየት አፈጻጸማቸውን ለመከታተልና ለማሻሻል እንዲረዳ የየወሩ የስራ ክንውናቸውን ወደ መረጃ ቋት እንዲገባ መደረጉን አስገንዝበዋል ፡፡