ክልሉ ከ 400 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ፕሮጀክቶች ፈቃድ ሠጠ

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ከ400  ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ፈቃድ  መሥጠቱን አስታወቀ ።

የክልሉ የኢንቨስትመንት ቢሮ የኢንቨስትመንት ማስፋፋያ ኃላፊ አቶ ክብረ ወሰን  መኩሪያ ለዋልታ እንደገለጹት የኢንቨስትመንት  ፍቃድ ከተሠጣቸው  ከ72  ፕሮጀክቶች ውስጥ  44  የሚሆኑት  በግብርና የተሠማሩ እንዲሁም የቀሩት  በማኑፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽንና  በአገልግሎት ዘርፍ የሚሠማሩ ናቸው ።

የቤኒሻንጉል  ክልላዊ መንግሥት በግብርና ዘርፍ ለሚሠማሩት ባለሃብቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ  መሬት ለመሥጠት እየሠራ ይገኛል ብለዋል አቶ ክብረወሰን ።

በቤኒሻንጉል ክልል በኢንቨስትመንት  ለሚሠማሩ ባለሃብቶች   በሚሠጠው ድጋፍ ምክንያት  በተለያዩ  የኢንቨስትመንት ዘርፎች  የሚሠማሩ  ባላሃብቶች   ቁጥር ከባለፈው የበጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ዕድገት አሳይቷል ።