ኢትዮጵያ በአፍሪካ የኃይል ገበያ ለመግባት የሚያስችላትን የመሥመር ዝርጋታ እያከናወነች ነው

ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ገበያ ዘልቃ ለመግባት የሚያስችላትን የኤሌክትሪክ ኃይል መሥመር ዘርጋታ እያከናወነች መሆኑን የኢትዮጵያ  ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ ።

የአትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንጂነር አዜብ አስናቀ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ወደ ከሱዳንና ከጅቡቲ ከተዘረጋው  የኤሌክትሪክ ኃይል መሥመር የተሻለ ኤሌክትሪ ኃይል የሚችሉ ተጨማሪ የመሥመር ዝርጋታና ጥናት እየተጠናቀቀ ነው ።

የኤሌክትሪክ  ኃይል በመሸጥ  የውጭ  ምንዛሬ ከማስገኘት ባሻገር ለቀጠናው አገራት ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች እንዳለው  ኢንጂነር አዜብ አስረድተዋል ።

እንደ እንጂነር አዜብ ገለጻ እስካሁን ድረስ  በአገሪቱ ከ4ሺህ ሜጋዋት በላይ ኃይል ማመንጨት መቻሉንና  በሁለተኛው  የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ማጠናቀቂያ ዓመት በአጠቃላይ 17ሺ ሜጋ ዋት  ለማመንጨት በዕቅድ ተይዞ እየተሠራ ነው ።

ከኢትዮጵያ ወደ  ኬኒያ እየተዘረጋ  ያለው  የኤሌክትሪክ  ኃይል  መሥመር  2 ሺህ ሜጋ ዋት መሸከም የሚችል መሆኑን የጠቆሙት እንጂነር አዜብ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታው በደቡብና ምስራቅ 12 አገራትን እንዲሁም የሰሜን አፍሪካ መካከለኛው ምስራቅና አውሮፓን በኃይል የማስተሳሰር ራዕይ እንዳለው ገልጸዋል ።

የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ቋት ዋና ጸሓፊ ሚስተር ሌቢ ቻንጉላ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የቀጠናውን ሀገራት በኃይል የማስተሳሰር ስራ አፍሪካን ከሌሎች ሀገራት ጋር እስከ ማገናኘት የሚዘልቅ በመሆኑ ለሀገራቱ ፍርጀ ብዙ ጥቅም ይሠጣል ብለዋል ።

ኢትዮጵያ ከውሃ  ፣ከነፋስ ፣ከፀኃይና ከእንፋሎት 60 ሺ ያህል ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት የሚያስችል እምቅ አቅም ያላት ሲሆን  ከዴሞክራቲክ  ሪፐብሊክ ኮንጎ በመቀጠል ከፍተኛ  የኤለክትሪክ ኃይል በማመንጨት አቅም ከአፍሪካ ሁለተኛ መሆኗን የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ ፡፡